በባህርዳር ከተማ ሃምሌ 20,2005 ዓ/ም በተካሄደ የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባ በኦዲት ክፍል ተመርምሮ
በቀረበው ሪፖርት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ተብሎ ከክልሉ ኗሪዎች የተሰባሰበው ገንዘብ የ 8 ሚልዮን ጉድለት ማሳየቱን ተገልጻል። ጉድለቱ
መታየቱን ሪፖርት ያቀረበው ኦዶተር ጉድለት መታየቱን መግለጽ የለብህም የሚል መመሪያና ማስፈራሪያ ተሰጥቶታል።
የተሰባሰበውን ገንዘብ ኦዲት ያደረገው ባለሞያ አቶ አለሙ ታፈሰ ሲሆን ኦዲት እንዲያደርግ የተሰጠውን ሃላፊነት
ለስርዓቱ ባለው ታማኝነት እንደሆነ አውቆ ጉድለት ቢታይም ጉድለት እንዳልተገኘበት አስመስሎ እኒድያቀርብ ካልሆነ ህዝቡ ገንዘቡ እደባከነ
ካወቀ ልግድቡ ማሰሪያ ማዋጣቱን እንደሚያቆም በመንግስትም ላይም ለዓመጽ ሊነሳሳ ስለሚችል ጉዳዩ አደገኛ መሆኑን ተገንዝቦ የተባለውን
እንዲፈጽም ተነግሮታል። ነገር ግን አቶ አለሙ ታፈሰ የተባለውን ለመፈጸም ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ ስራውን እንዲያቆም ተደርጎ በምትኩ
ሌላ ሰው መመደቡን ለማወቅ ተችሏል።