በዞኑ የንጹን የመጠጥ ውሃ መስመር ለመዘርጋትና የከተማ የውስጥ ለውስጥ መንገድ የአስፋልት ንጣፍ ለማንጠፍ በሚል ከአከባቢው ኗሪዎች ከሁለት ዓመት በፊት የተሰባሰበው ገንዘብ በስራ
ላይ ሳይውል በመጠፋፋቱ ኗሪው ህዝብ ሃምሌ 21,2005 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱ ለመረዳት ተችሏል።
የዞኑ ህዝብ ባካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የግል ፍላጎታችንን በመግታት ያዋጣነውን ገንዘብ አከባቢያችን በማልማት
ተጠቃሚዎች ለመሆን እንጂ የባለስልጣናትን ኪስ ለመሙላት አይደለም በማለት ተቃውማአቸውን በመግለጽ ላይ እያሉ በቦታው የተኘው የዞኑ
አስተዳደር አቶ ፈቃዱ አለማዩሁ በርግጥ ገንዘብ አዋጥታችሃል ነገር ግን ለሌላ የመንግስት ስራ ስለዋለ ቀጣዩ በጀት ሲመደብልን የጠየቃችሁትን
ጥያቄ ምላሽ ያገኛል የሚል ሰንካላ ምክንያት እንደሰጣቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ሰላማዊ ሰልፉን የመሩትና ያስተባበሩት የአከባቢው ኗሪዎች
1-አቶ አስፋው ተበጀ ያገር ሽማግሌ
2-አቶ አሕመድ ናስር የሙስሊም ተወካይ
3-ወ/ሮ ዉብ አለም ይታገሱ የዞኑ የሴቶች ማህበር ኅላፊ ናቸው።
የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪ ኮሞቴ በዞኑ መስተዳድር የተሰጠው ምላሽ ስላልተደሰቱ እስከ ክልል ድረስ በመሄድ
ክስ እንደሚመሰርቱ ገልጸዋል።