በደረሰን ዘገባ መሰረት የአደባይ ኗሪዎች ለእርሻ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬታቸውን መታገድ አስመልክተው ሃምሌ
23,2005 ዓ/ም ባደረጉት ስብሰባ ሰረና እየተባለ በለምዶ ሰረና እየተባለ የሚጠራውን ለከብቶቻችን ግጦሽ የምንጠቀምበት መሬት
የእርሻ መሬታችን ከተወሰደብን እንዴት ነው ኑራችን እምንመራው የተወሰነውን እንኳ ተውሉን በማለት በኗሪዎቹ የቀረበ ሃሳብ ተቀባይነት
እንዳላገኘ ቷውቋል።
የከባቢው የመስተዳድር አካላት የአደባይን ህዝብ ሰብሰባ ጠርጠው ሃሳባቸውን በጉልበት ለማዝፈጸም ቢሞኩሩም
ኗሪው ህዝብ ያቀረብነውን ሃሳብ ተቀብላችሁ መፍትሄ እስካልሰጣችሁን ድረስ እኛም የናንተን ሃሳብ ለማድመጥ ገቃደኞች አይደለንም በማለት
ስብሰባውን ረገጠው እንደወጡ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።