Friday, August 2, 2013

በዓዲግራት ከተማ የሚገኙ የህወሓት ካድሬዎች ወጣቱን በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ለማደራጀት በሚል ሰበብ ከመንግስት ካዝና ገንዘብ ወጪ በማድረግ ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ቷውቋል።



የትግራይ ምስራቃዊ ዞን የአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ሃላፊ አቶ ዋሲሁን አበበ የተባለ ባለስልጣን በዓዲ ግራት ከተማ የሚገኙ ትምህርታቸውን አጠናቀው ስራ እጥ የሆኑ ወጣቶችን ስራ ፈጥረው እራሳቸውን እንዲለውጡ የፋይናንስ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል በሚል በወጣቶቹ ስም ከመንግስት ካዝና ሦስት ሚልዮን ብር ወጪ በማድረግ ከአከባቢው ለመሰወር ሲሞክር በህዝብ ትብብር በቁጥጥር ስር በዋሉን ለማወቅ ተችሏል።
ወንጀለኛው የስርዓቱ ታማኝ የነብረና በሃላፊነት ተመድቦ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን ከበላይ ሃላፊዎቹ ጋር በመመሳጠር ቀደም ሲልም ተመሳሳይ ወንጀል በተደጋጋሚ ይፈጽም የነበረ ነው። ግለሰቡ በተለያየ ጊዜ ከህዝብ ክስ ቢቀርብበትም የሚመለከታቸው አካላት የህዝቡን ቅሬታ ስላጣጣሉት ሙቹ ሁኔታ ተፈጥሮለት በማን አብኝነት እንዳሻው የህዝቡን ገንዘብ ሲዘርፍ ቆይቷል።