Friday, August 2, 2013

የአ/አበባ ከተማ የመስተዳድር አካላት ከውጭ ከመጡ ባለሃብቶች የሚሰጣቸውን በርካታ የመደልያ ገንዘብ ሲሉ ለዓመታት በከተማዋ በአቅማቸው ቤት ሰርተው ሲኖሩ የነበሩ ዜጎችን በህገወጥ መንገድ እንዳፈናቀሏቸው ቷውቋል።



የኮልፌ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ ጌታቸው በክልፈ ከተማዋ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ እንደአቅማቸው ቤት ሰርተው ህይወታቸውን ሱመሩ የነበሩ ኗሪዎችን ያላችሁበትን አከባቢ ለልማት ስለሚፈለገና ከውጭ ለመጡ ባለሃብቶች ስለሚሰጥ እናንተ ካላችሁበት ደሳሳ ጎጆ ወጥታችሁ በሌላ ተለዋጭ ቦታ የተሻለ ቤት ተሰርቶ ከተጨማሪ ገንዘብ ጋር ይሰጣችሃል በማለት በማታለል ለዓመታት የኖርበትን ቤት አፍርሰው እንዲወጡ አድርጓል፣ አስተዳዳሪው በተጭበረበረ ሰነድ መሬቱን ለውጭ ባለሃብቶች በማስረከብ 6 ሚልዮን ብር በመቀበል ለግል ጥቅሙ አውሎታል።
 በተጭበረበረ ሰነድ መሬት በህገወጥ መንገድ የገዙ ከውጭ የመጡ ኢቶጵያዊያን ባለሃብቶች ስም፣-
1-አቶ ይኩኖ አለባቸው
2-ወ/ሮ ሓያት ሓጎስ
3-አቶ ክፍሉ ሃ/ሚካኤል ሲሆኑ የክፍለ ከተማዋ አስተዳዳሪ የሚፈለጉት ቦታ መዘጋጀቱንና መረከብ እንደሚችሉ በመግለጽ ሃምሌ 18,2005 ዓ/ም በማጭበርበር  ያገኘውን 6 ሚልዮን ብር በመያዝ ሳውዲ አረቢያ መግባቱን ቷውቋል።
ቤታቸው በህገ ወጥ መንገድ የፈረሰባቸው የአከባቢው ኗሪዎች በአሁኑ ጊዜ አውላላ ሜዳ ላይ ወድቀው ወቅቱ የክረምት ወራት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ዝናብ ብርድና ጸሃይ እየተፈራረቀባቸው በከባድ ችግር ላይ ይገኛል።