በያዝነው ሳምንት ብቻ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙባቸው በርካታ ወጣቶች ኢህአዴግ በሚከተለው ብልሹ
አሰራር ምክንያት በሃገራቸው በሰላም ሰርተው መኖር ስላልቻሉ የኢህአዴግን ስርዓት በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል በመፋለም ከስልጣኑ
አሽቀንጥሮ ለመጣል ከትህዴን ጎን ተሰልፈው ለመታገል ወስነው ድርጅቱን የተቀላቀሉ ናቸው።
ወደ ትህዴን ከተቀላቀሉ ወጣቶች መካከል፣-
1. ሓጎስ ዘርአስ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ወልቃይት ወረዳ ፤ ሰላም መንደር
2. ጸሃየ ታፈሰ፤ከምዕራባዊ ዞን ፤ ወልቃይት ወረዳ ፤ ዓዲ ጋባ መንደር
3. አማኑኤል ግደይ፤ከሰ/ምዕራብ ዞን፤ታሕታይ አድያቦ ወረዳ፤ዓዲ-ተለዖም መንደር
4. ኣብረሃ ባሻ ኣበራኣ ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ከቃፍታ ሑመራ ውረዳ ፤ ዓዲ-ጎሹ መንደር
5. ተወልደ ኪሮስ ፤ ከማእከላዊ ዞን ፤ወርዒ ለኸ ወረዳ ፤ መዕኸል መንደር
6. በረኸት ታፈረ ፤ ሰ/ምዕራብ ፤ ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ ደጓዓለ መንደር
7. ፋንታሁን ገ/ሚካኤል ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ጸገዴ ወረዳ ፤ ዳንሻ ከተማ
8. ባቤ ደብሴ ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ጸገዴ ወርዳ ፤ ዳንሻ ከተማ
9. ሃፍቶም ጸጋይ፤ከምስራቃዊ ዞን፤ከጉለ መኸዳ ወረዳ፤ዛላምበሳ መንደር
10. ጠዓመ በርሀ ፤ማእከላዊ ዞን ፤ጣንቋ ኣበርገለ ወረዳ ፤ ሙሴ መንደር
11. ኪዳነማሪያም ተጠምቀ ፤ ማእከላዊ ዞን ፤ ታሕታይ ማይጨው ወርዳ ፤ ድምብላ መንደር
12. ሴይፉ አለሙ ፤ ከደቡብ ክልል ፤ ገና ወረዳ
13. አታኽልቲ አክሊሉ ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ጸገዴ ወረዳ ፤ ከዳንሻ
14. ጉዕሽ ታፈረ ፤ ከሰ/ምዕራብ ዞን ፤ ታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ ከ ዓድ-ጸጸር መንደር
15. ቢንያም በርሀ ፤ ከማእከላዊ ዞን ፤ ጣንቋ አበርገለ ወረዳ ፤ ከሰላም መንደር
16. ተወልደ ሓድሽ ፤ ከደቡ ዞን ፤ ሕንጣሎ ዋጅራት ወረዳ
17.ተኽላይ ደስታ ፤ ከሰ/ምዕራብ ዞን ፤ ከታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ ዓዲ-ጸጸር መንደር
18.መለስ በርሀ ፤ ከምዕራባዊ ዞን ፤ ሰቲት ሑመራ ወረዳ ፤ ቀበሌ-02
19. አታኽልቲ ዘርኡ፤ከማእከላዊ ዞን፤ከወርዒ ለኸ ወረዳ፤ ከአዝመራ መንደር
20.ተማመን ባዝና ፤ ከኦሮሚያ ክልል ፤ ከጅማ ወረዳ
21. ሚኪኤለ ተ/ሚካኤል ፤ ከማእከላዊ ዞን ፤ ከመረብ ለኸ ወረዳ ፤ ከማይወይኒ መንደር
22. ሕጉስ፤ ከማእከላዊ ዞን ፤ ላዕላይ ማኡጨው ወረዳ ፤ ማይ-ወይኒ መንደር
23. ደመቀ አታሉ ፤ ከአማራ ክልል፤ ከደቡብ ጎንደር ዞን፤ ደብናብ ወርዳ ፤ አጊሳ ቀበሌ
24. ሙላው ደመቀ፤ከ ሰ/ምዕራብ፤ ከጸለምቲ ወረዳ ፤ መድሃኔ ዓለም መንደር
25. ተስፋይ ታደሰ ፤ ከሰ/ምዕራብ ዞን ፤ ከታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ ዋዕላ ንህቢ መንደር
26. ተኸለ ሓድጉ፤ ከሰ/ምዕራብ ዞን፤ መደባይ ዛና ወረዳ፤ ኩሉ-ፈርሃ መንደር
የሚገኙባቸው ሲሆን አስተያየታቸውን ከሰጡ
ወጣቶች መካከል ወጣት ተሻለ ሓድጉና ጉዕሽ ታፈረ ኢህአዴግ በህዝቡ ላይ የሚፈጽመውን በደል አስመልክተው ሲናገሩ ወገንና ገንዘብ
የሌለው ማንኛውም ዜጋ ተጨቁኖ እንደሚኖር በተለይ ወጣቱ በሃገሩ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ የመታወቅያ ወረቀትን በመከልከልና በርካታ
የፍተሻ ኬላዎችን በመክፈት ከየት መጣህ? ፤ የት እየሄድክ ነው? በሚል ሰበብ በርካታ ወጣቶች ምንም ወንጀል ሳይኖራቸው በየእስር
ቤት ታስረው እንደሚማቅቁና የእርሻ መሬት በተመለከተም ፍትሃዊ ክፍፍል እንደሌለ ገልጸዋል።
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የ4ኛ ዓመት ተማሪ የነበረ ወጣት ሴይፉ አለሙና በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪውን
ሲያጠና የነበረው ኪዳነማሪያም ተጠምቀ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየትም በኢህአዴግ ስርዓት አንድ ተማሪ በዩኒቨርሲቲው ገብቶ ከተመረቀ
ብሁዋላ በዉጤቱ ተወዳድሮ ስራ የሚያገኝበት እድል ስለሌለ አብዛኛው ተማሪ ቅድሚያ የሚሰጠው ለትምህርቱ ሳይሆን በጥሩ ስራ የሚያስመድበው
ባለስልጣን ፍለጋ ላይ ነው ሲል ገልጸዋል።