በካንሰር በሽታ የተጠቁ በጥቁር አምበሳ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ሆስፒታሉ የሄዱ በሽተኞች
እንደሚሉት ከሆነ ሆስፒታሉ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰቡ ክፍሎችን በማጉላላትና የህክምና አገልግሎት በአግባቡ ሳይሰጥ ለባለስልጣናት
ቤቶሰቦችና ባለሃብቶች ያለምንም ውጣ ውረድ በሰዓታት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ህክምና እንዲያገኙ ይደረጋል ሲሉ በሆስፒታሉ አሰራር
ላይ ያላቸውን ቅሬታ ይገልጻሉ።
በሆስፒታሉ በቂ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ስላልቻሉ በሚደርሲባቸው መጉላላት ምክንያት በዚሁ በሽታ የሚሞቱ
ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በሽተኞቹ በሚሰጣቸው ማለቅያ የሌለው የህክምና ቀጠሮ ከ 6 ወራት
በላይ ተመላልሰው የህክምና አገልግሎት ማግኘት የማይቻልበት ሁኔታ ነው ያለው።