Saturday, August 17, 2013

የወልዲያ ከተማ የስፖርት ኮሚሽን ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ጌታሁን ለከተማዋ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና እንዲሆን ከህዝብ የተዋጣውን ገንዘብ በጀት ይዞ ከከተማዋ ተሰወረ።




የወረዳዋ የስፖርት ኮሚሽን ሃላፊ አቶ ኤፍሬም ጌታሁን ለከተማዋ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና በሚል ነሃሴ 5,2005 ዓ/ም የተመደበው ከ 200 ሽህ በላይ በጀት ለግል ጥቅሙ ያዋለው ሲሆን በአንዳንድ ተቆርቃሪ ወገኖች ግለሰቡ ገንዘቡን ማባከኑን ተረጋግጦ ወደ ፍርድ ቀርቦ ነበር ። ነገር ግን በሙስና የተጨማለቁት የኢህ አዴግ ካድሬዎች ግለሰቡን በዋስ በማስፈታት ከከተማዋ እንዲሰወር ማደረጋቸውን ቷውቃል።
ችሎቱን ያስቻሉ ዳኞቹ ከስርዓቱ ካድረዎች ጋር እጅና ጓንት በመሆናቸው ግለሰቡ የፈጸመው ጥፋት ከባድ መሆንን እየታወቀ ከተዘረፈው ገንዘብ ተካፋዮች ስለሆኑ ብቻ ወንጀለኛው የዘረፈውን ገንዘብ ሳያስረክብ በዋስ እንዲፈታ አድርገዋል።