Saturday, August 17, 2013

በሰለኽለኻ ከተማ የሚገኙ ነባር የፖሊስ አባላትና ታጋዮች የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ሰፍ አካሄዱ።




እነዚህ የከተማዋን ኗሪ ህዝብ በማደራጀት ነሃሴ 3,2005 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ ያካሄዱ ነባር ታጋዮች የሰላማዊ ሰልፉን ዓላማ ሲገልጹ እኛ የትግራይ ህዝብ ባደረገው የትጥቅ ትግል ሁለንተናዊ መስዋእትነት በመክፈል የደርግን ስርዓት ውድቀት ያረጋገጥን ታጋዮች ነን። ነገር ግን ስርዓቱ ስልጣን ከተቆጣጠረ ብሁዋላ ያለምንም መቋቋምያ እኛን ማባረሩ እንዳይበቃ በላባችን ጥረን ግረን የሰራነውን መኖሪያ ቤቶቻችን ያለ ምንም ካሳና ተለዋጭ መሬት በማፍረሱ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ መሆኑን ገልጸዋል።
በሰላማዊ ስልፉ በርካታ የከተማዋ ኗሪዎች የተሳተፉ ሲሆን የወረዳዋ አስተዳደር አቶ ተስፋይ ብርሃነ ያቀረባችሁት ጥያቄ ዛሬም ሆነ ነገ ተቀባይነት አይኖረውም ሲል በንቀት ምላሽ መስጠቱ እንዳይበቃ በዚህ ጉዳይ ምንም ዓይነት አቤቱታ መስማት አንፈልግም አርፋችሁ የተባላችሁትን ፈጽሙ በማለት ኗሪውን ለማስፈራራት መሞከሩ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።