Friday, August 2, 2013

በመቐለ ከተማ ዓረናና መድረክ በጠሩት ስብሰባ ሙሁራንን ጨምሮ በርካት ህዝብ መሳተፉቸውን ቷውቋል።



በመድረክና ዓረና አዘጋጅነት በመቐለ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሃምሌ 14,2005 ዓ/ም የተካሄደው ስብሰባ ዋና ዓላማው በጉልበት ስልጣን ተቆጣጥሮ በህዝቡ ላይ በደል እያደረሰ ያለውን ጸረ-ህዝቡ የኢህአዴግ ስርዓት ከስሩ መንግሎ ለመጣል ሲሆን በስብሰባው ከ 1500 በላይ የሚሆኑ የዩኒቨርሲቲው ሙሩቃን ተማሪዎች ነባርና አዳዲስ የዓርና-ትግራይ አባላትና ሌሎች ድርጅቱን የሚደግፉ የህብረተሰቡ አባላትና የኢህአዴግ ካድሬዎች ሳይቀር ተገኝተዋል፣ ስብሰባው በጣም ስኬታማና እንደነብረ ለማወቅ ተችሏል።
ስብሰባው በወቅቱ የመድረክ ሊቀ-መንበር አቶ ጥላሁን እንዳሻውና በዓረና-ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት የተመራ ሲሆን ዴሞክራሲያዊ ፤ ነጻና አሳታፊ እንደነበረና ከስብሰባው ተሳታፊዎች ህዝቡ በኢህአዴግ አገዛዝ ተማርሮ ከጎናቸው ተሰልፎ እያለ ለምን ይህንን ሃይል ተጠቅማችሁ አዲስ ስርዓት እውን እንዲሆን የሚፈለገውን እንቅስቃሴ አታደርጉም የሚል ጥያቄ ቀርባል።
  ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በስብሰባው የተገኙ ተሳታፊዎችም መድረክ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ተገኝቶ ተመሳሳይ ስብሰባ በማካሄድ ህዝቡን እንዲያወያይ መጠየቃቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።