Wednesday, August 7, 2013

ከዓዲ-ጎሹ ከተማ ወጣ እንዳለች የመገልበጥ አደጋ በደረሰባት አንዲት ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍሮ የነበረ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በተተኮሰበት ጥይት ተገደለ።




በትግራይ ምዕራባዊ ዞን ዓዲ-ጎሹ አከባቢ መነሻው ባልታወቀ ምክንያት የመገልበጥ አደጋ በደረሰባት አንዲት ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍሮ ሲጓዝ የነበረና ከአደጋው የተረፈ ፍጹም የተባለ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በሁለት ጥይት አንገቱ ላይ ተመትቶ መገደሉንና እስካሁን ድረስ የገዳዮችን ማንነት እንዳልታወቀ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ሟቹ በተገደለበት ወቅት ከነ ሙሉ ወታደራዊ ትጥቁ የነበረ ሲሆን ታጥቆት የነበረው ትጥቅም ወዲያውኑ በገዳዮቹ ተወስዳል ። በግለሰቡ ላይ የተፈጸመው ግድያ በኢህአዴግ ስርዓት በተማረሩ ዜጎች የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ አንዳንድ የአከባቢው ኗሪዎች ይናገራሉ።
የኢህአዴግ ስርዓት የህዝቡን ተቃውሞ በሃይል ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ባለበት በአሁኑ ጊዜ በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ በተደጋጋሚ ከህዝቡ የሚሰነዘር ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን የሚታወቅ ነው።