Wednesday, August 7, 2013

በአገሪቱ ባለው ከፍተኛ የስራ-እጥነት ችግር ምክንያት ወደ ስደት የሚያመሩ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

ከሃገሪቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ስደት የሚያመሩ ዜጎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን ሃምሌ 24,2005 ዓ/ም ወደ ዓረብ ሃገር ለመሄድ በአፋር ክልል በኩል በሰሌዳ ቁጥሩ 62597 ሸራ በለበሰ አንድ ተሽከርካሪ ተጭነው ሲጓዙ የነብሩ ዜጎች ስድስት ሰዓት ከፈጀ አስቸጋሪ ጉዞ ብሁዋላ በአየር እጦትና የአከባቢውን ከፈተኛ ሙቀት መቋቋም ተስኗቸው የመኪናውን ሸራ በመግለጣቸው በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ከትግራይ ክልል ተነስተው ለደላሎችና ለትራንስፖርት በሽዎች የሚቆጠር ገንዘብ በመክፈል ወደ ስደት ሲያመሩ የነበሩ ወጣቶች ተማሪዎች ሲሆኑ ብዛታቸው 45 ይደርሳል ። ከተያዙበት ቀን ጀምሮ ማይጨው በሚገኘው እስር ቤት ታጉረው በስቃይ ላይ ይገኛሉ።