በደረሰን ዘገባ መሰረት ግጭቱ የተከሰተው በሱዳንና ኢትዮጵያ ድንበር ‘ዓላው’ በተባለ አከባቢ ‘ግድማ’
በተባለ ልዩ ቦታ ሲሆን የግጭቱ መንስኤ የእርሻ መሬት ይዞታ ነው። እስካሆን ድረስ ችግሩ እንዳልተፈታ ለማወቅ ተችሏል።
እንዲህ ዓይነት ግጭት አሁን የጀመረ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ሲከሰት የነበረ ነው፣ የኢህ አዴግ
መንግስት ለሃገርና ለህዝብ ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ መሰረታዊ መፍትሄ ማድረግ ሲገባው ለፖለቲካ ፍጆታ ሲል የአገሪቱን መሬት ለሱዳን
አሳልፎ በመስጠቱ በሁለቱም አገሮች ድምበር በሚገኙ ኗሪዎች መካከል የነበረው ግጭት ተባብሶ እንዲቀጥል ምክንያት ሆናል ሲሉ የአከባቢው
ኗሪዎች ይናገራሉ።
የኢህአዴግ መንግስት የመላው የኢትዮጵያ ህዝብን ያስቆጣ ከ 1600 ኪ/ሜ በላይ ከሰሜን እስከ ምእራብ ጫፍ
ከ 40-60 ኪ/ሜትር ወደ ውስጥ የሚገባ ሰፊ መሬት ለሱዳን አሳልፎ እንደሰጠው የሚታወቅ ነው።