Friday, August 2, 2013

በታሕታይ ማይጨው ወረዳ ለህዝባዊ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን ግዥ እንዲውል የተመደበው በጀት የወረዳዋ ግዥና ገንዘብ ያዥ ጋር በመመሳጠር ለግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት ቷውቋል።



በትግራይ ማእከላዊ ዞን በታሕታይ ማይጨው ወረዳ ለወረዳው እርሻና ልማት ጽ/ቤት ተብሎ የተመደበውን በጀት ጉዕሽ የተባለ የመ/ቤቱ ሃላፊ ከመ/ቤቱ የእቃ ግዥ ሃላፊ ጋር በመመሳጠር ለንብረት መግዣ በሚል ሃምሌ 12,2005 ዓ/ም አንድ ሚልዮን ብር ወጪ በማድረግና የተጭበረበረ ሰነድ በማስረጃነት በማቅረብ ገንዘቡን መዝረፋቸውን ቷውቋል።
በህገወጥ መንገድ ወጪ የሆነው ገንዘብ ብሁዋላ በተደረገው ፍተሻ በተጭበረበረው ሰነድ ተገዝቷል የተባለው ንብረት ብላመገኘቱና የቀረበው ሰነድም ህጋዊ እንዳልሆነ ተረጋግጦ አንድ ሚሊዮን ብር አለአግባብ ወጪ ሆኖ ሁለቱም ግለሰቦች እያንዳንዳቸው አምስት መቶ ሽህ ብር በመውሰድ መካፈላቸውን ቷውቋል።
ወምጀለኞቹ ሃላፊነት በሚሰማቸው የመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ትብብር በህግ ቁጥጥር ስር ቢውሉም በወረዳና በዞን የሚገኙ ከወንጀለኞቹ ጋር ግንኝነት ያላቸው ባለስልጣናት ግለሰቦችን ለማስፈታት እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ቷውቋል።