በዞኑ የሚታዩ የመንገድ ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ለማቃለል የአከባቢው ኗሪ በተቻለ መጠን
አቅማቸው አስተባብረው በመንቀሳቀስ ያዋጡትን በርካታ ገንዘብ የዞኑ አስተዳዳሪ የተረከበው ቢሆንም ዛሬ ነገ ስራው ይጀመራል እየተባለ
በመጓተቱ ቅር የተሰኘው የአከባቢው ኗሪ ሃምሌ 19,2005 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዱን ለማወቅ ተችሏል።
ህዝቡ ለመሰረተ ልማት እንዲውል ያዋጣነው ገንዘብ የት ገባ ? ስራውን መስራት ካልቻላችሁ ገዘባችን መልሱሉን
በማለት በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቀ ሲሆን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ጸጉ ጌጡ ከተዋጣው ገንዘብ 2.7 ሚልዮን ብር ለግል ጥቅሙ እንዳዋለው
ቢታወቅም የሚጠይቀው አካል አልተገኘም ፣ ህዝቡ ላነሳው ጥያቄም እስካሁን ድረስ የተሰጠ ምላሽ የለም።