Sunday, August 4, 2013

የሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የመስተዳድር አካላት በከተማዋ አሸባሪዎች ሰርገው ገብተዋል በሚል ምክንያት የከተማዋን ኗሪዎችን ሰብስበው ማናገራቸውን ታወቋል።




በትግራይ ክልል ፤ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ሃምሌ 24 እና 25,2005 ዓ/ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የተካሄደው ስብሰባ አጀንዳ በከተማዋ አሸባሪዎች ሰርገው ገብተዋል የሚል ሆኖ ህዝቡ ጉዳዩን ተገንዝቦ ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ሽብር ፈጣሪዎችን መንጥሮ ማስወጣት አለበት ፥ እንቅስቃሴውንም ከአሁኑ ሰዓት መጀመር አለበት የሚል መሆኑን ቷውቋል።
በስብሰባው የተገኙ የከተማዋ ኗሪዎች ቀደም ሲል ከአክራሪነት ጋር የተያያዙ እንግዳ የሆኑ አንዳንድ ችግሮች መታየታቸውን በተደጋጋሚ ስናቀርብ ቆይተናል ፥ ነገር ግን ሕሊናችሁ ከኗሪው ህዝብ የሚቀርቡላችሁ ነገረችን ለማድመጥ ዝግጁ አይደለም ። አሁን ችግሩ እየተባባሰ ከመጣ ፤ የሃገሪቱን ባንዴራ እስከ መቅደድና ማቃጠል ከተደረሰ ብሁዋላ እኛን ወደ ሰብሰባ መጥራት ምን ፋይዳ አለው በማለት ስብሰባውን ሲመሩ ለነበሩ የስርዓቱ ባላለስልጣናት ተቃውማቸውን በቁጣ መግለጻቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
       የከተማዋ ኗሪዎች በመልካም አስተዳደር እጦት ምክንያት በከተማዋ ከፍተኛ የመሰረት ልማት ችግር አለ ህዝብ ችግሮችን ከመንግስት ጋር ተባብሮ ለመፍታት በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርብም የሚያደምጥ አካል አልተገኘም። በትክክል ህዝብን ለማገልገል የቆማችሁ ከሆነ በትጥ ትግሉ ጊዜ እንደነበረው ሁሉ ከህዝብ ጋር በመቀራረብ እየተመካከራችሁ ስሩ ። ካልሆነ በናንተ ላይ የሚያነጣጥር ችግር በተከሰተ ቁጥር በአክራሪዎች ስም ስልጣናችሁን ለማስጠበቅ የምታደርጉት እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም ሲሉ በመድረኩ እንደገለጽላቸው ለማወቅ ተችሏል።