በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋታ አለቡና እንዳሻው ታፈሰ የተባሉ ሁለት የፌደራል አባላት ሃምሌ 20, 2005 ዓ/ም
ሌሊት ተገድለው ተገኝተዋል። ከግድያው በስተጀርባ የማን እጅ እንዳለ ለጊዜው ባይታወቅም ግድያው ከመፈጸሙ አንድ ቀን ቀደም ብሎ
ዓርብ ዕለት በሙስሊሙ ህብረተሰብ ከተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር የተያያዘ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ።
የኢትዮጵያ ርእሰ ከተማና የአፍሪካ መዲና መሆናን የሚነገርላት አ/አበባ የኢህአዴግ ስርዓት መንግስት በሚከተለው
ጸረ-ህዝብ አካሄድ ስጋት ነግሶባት የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ሰላምና ነጻነት ተነፍጎት ማንኛውም እንቅስቃሴው በስርዓቱ የደህንነትና የፌደራል
ፖሊስ አባላት ክትትል ስር ሆኖ እለታዊ ስራውን በአግባቡ መከወን መቸገሩን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።