እንደ ከተማዋ ነጋዴዎች ቅሬታ ፤ የግብር አከፋፈል ስርዓቱ በተግባር ሲታይ ከኢህአዴግ ስርዓት ጋር ለሚሞዳሞዱት
ሙሰኛ ነጋዴዎችን የሚያበረታታ ሲሆን የኢህአዴግ ደጋፊ ላልሆኑና ህግን ተከትለው በቅንነት ለሚሰሩ ነጋዴዎች ደግሞ ከስራ ውጭ የሚያደርግ
ነው ። ይኸውም በጉቦና በጥቅማጥቅም ከባለስልጣናት ጋር የተሳሰሩ ነጋዴዎችን መክፈል ከሚገባቸው እጅግ ዝቅተኛ ግብር በማስከፈል
ጉቦ ለማይሰጡና ከባለስልጣናት ጋር በጥቅማጥቅም ያልተሳሰሩ ባለሃብቶችን ደግሞ መክፈል ከሚገባቸው በላይ ከፍተኛ ግብር በመጫን ከስራ
ውጭ እንዲሆኑ ይደረጋል።
እንዲህ ባለው ፍርደ ገምድል አሰራር የገዥው ፓርቲ ደጋፊዎች ስላልሆኑ ብቻ እንደወንጀለኛ ተቆጥረው ከንግዱ
ዓለም ለማስወጣት ሆን ተብሎ መክፈል ከሚገባቸው በሚልዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ግብር ስለተጫነባቸው በርካታ በከተማዋ የሚኖሩ ህጋዊ
ባለሃብቶችን የንግድ ድርጅቶቻቸውን ዘግተው ስራ ፈት ሆነዋል።
ባለሃብቶቹ በመንግስት የተጣለብን ከፍተኛ ግብር ለመክፈል አቅሙ የለንም። በአሁኑ ጊዜ አቤት የምንልበት
ስርዓት ስለሌለ ገዥው ፓርቲ እንደለመደው በማን አለብኝነትን ንብረታችንን ሸጦ መውሰድ ይችላል ሲሉ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ
በምሬት መግለጻቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።