እነዚህ በማህበር ተደራጅተው መንቀሳቀስ ከጀመሩ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ከማምረት ተላቀው በማሽን እንድታመርቱ
ይደረጋል የሚል ከመንግስት የተገባላቸውን ቃል መሰረት በማድረግ የጦር ጉዳተኞቹ በሰባት ማህበራት እራሳቸውን በማደራጀት ሲንቀሳቀሱ
ከቆዩ ብሁዋላ ቃል የተገባላቸውን ማሽን እንዲሰጣቸው ለመንግስት ጥያቄ አቀረቡ ፥ ነገር ግን መንግስት የተገባላቸውን ቃል ባለማክበር
የምትፈልጉትን ማሽን በገንዝባችሁ እራሳችሁ ግዙ የሚል ምላሽ እንደሰጣቸው የማህበሩ አባላት ይናገርሉ።
የጦር ጉዳተኞቹ እኛ የአካል ጉዳተኞች ስለሆንን ፤ በባህላዊ መንገድ የወርቅ ማምረት ስራም ከፍተኛ የጉልበት
ስራን የሚጠይቅ ነውና መንግስት ችግራችን ተገንዝቦ የገባልንን ቃል በመጠበቅ የሚያስፈልገንን ማሽን ሊገዛልን ይገባል በማለት እስከ
ክልል ድረስ በመሄድ በተወካዮቻቸው በኩል በመጠየቅ ላይ ናቸው።