Tuesday, August 13, 2013

በአ/አበባ ከተማ በፖሊስ አባላትና በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት በርካታ የፖሊስ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ።




የእስልምና እምነት ተከታዮች ነሃሴ 02,2005 ዓ/ም በአ/አበባ ከተማ ፤ በቦሌ ክ/ከተማ ፤ መርካቶና ጎተራ አከባቢ የተነሳሳውን ተቃውሞ በአፈ ሙዝ ለመበተን ወደ ቦታው የደረሱ የፖሊስ አባላት ሰፍልፈኞቹ ባደረሱባቸው ጥቃት በርካታ የፖሊስ አባላት ቆስለው በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ቷውቋል።
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታሉ ተኝተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ካሉት የጸረ-ህዝቡ ስርዓት የፖሊስ አባላት መካከል አድማሱ ሃይለ ፤ ነብያት ታደሰ ፤ መሓመድ ፋራህና ጽጌ ታደሰ የተባሉ የፖሊስ አባላት ይገኙባቸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ በደሴ ከተማ የሚገኙ የሙስሊም ማህበረሰብ መንግስት በሃይማኖት ውስጥ እጁን በማስገባት መስጊድ በመሄደ ጸሎት እንዳናደርስ አሸባሪዎች ናችሁ በሚል ሰበብ የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራት ጥቃት እያደረሱብን ስለሆነ እቤታችን ሆነን ጸሎት ለማድረግ ተገደናል ሲሉ ያማርራሉ።