Sunday, September 22, 2013

በሱዳን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሃላፊዎች በኢምባሲው አለአግባብ ለባከነው ከ 50 ሽህ ብር በላይ ገንዘብ በኢምባሲው የበታች ሰራተኞች ላይ ለማላከክ እየሞከሩ ነው።



በካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ተመድበው በስራ ላይ የሚገኙ ሃላፊዎች በስራቸው የሚገኙ የበታች ሰራተኞችን በመሰብሰብ በኢምባሲው ከ 50 ሽህ ብር በላይ ገንዘብ አለአግባብ መውጣቱንና ለዚህም ተጠያቂዎቹ እናንተው ናችሁ በማለት ጥፋቱን በሰራተኛው ላይ ለማላከክ ሞክረዋል። ነገር ግን ሰራተኞቹ ችግሩ የተፈጠረው እራስ ወዳድ በሁኑ የኢምባሲው ሃላፊዎች እንጂ በሰራተኛው አይደለም ሲሉ ተቋውማቸውን ገልጸዋል።
በኢምባሲው ከሚገኙ ሃላፊዎች መካከል አንዱ ሃፍቶም የተባለ የኢምባሲው ስራ አስከያጅ ሲሆን እሱ ካሁን ቀደም በተደጋጋሚ አለአግባብ ገንዘብ ወጪ በማድረግ የሚታወቅ ሰው ነው ፥ ነገር ግን ግለሰቡ ባጠፋው ጥፋት ስላልተጠየቀ አሁንም ከሌሎች ሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ለእርዳት እንዲውል ከተሰባሰበው ገንዘብ 50 ሽህ ብር አለአግባብ ማንሳቱን በኢምባሲው የሚገኙ ሃላፊዎች ምን ያህል በሙስና መዘፈቃቸውን የሚያመለክት ነው ።
በኢምባሲው ከሚገኙት እጅግ በሙስና ከተጨማለቁት ስታፍ አባላት መካከል የኢምባሲው ስራ አስከያጅ አቶ ሃፍቶም ፤ አቶ ሚካኤልና አቶ አበበ ይገኙባቸዋል ። አቶ አበበ የአምባሳደሩ ሾፌር ሲሆን በካርቱም በድብቅ በሚሰሩ ጫት ቤቶች ጫት ሲቅምና ዊስኪ ሲጨልጥ እንደሚታይ የከተማዋ ኗሪዎች ይናገራሉ።