በሸራሮ ከተማ የሚገኙ በመንግስት ባለስልጣና የተመራ በህንጻ ኮንስትራክሽን የተደራጁ ማህበራት ሰራተኞች
ማእከል ያደረገ ከመስከረም 5,2006 ዓ/ም ጀምሮ ተከታታይ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ከዓመት ከመንፈቅ በፊት ያቀረቡትን
ጥያቄ እስካሁን ድረስ ስላልተመለሰላቸው የኢህአዴግ ስርዓት እኛን የሚፈልገን የስርዓቱ ደጋፊዎችና አገልጋዮች እንድንሆን እንጂ እንደ
ዜጋ መብታችን እንዲከበር አይደለም በማለት ሻምበል ብርሃነ የተባለ በአከባቢው ህዝብ ተሰሚነት ያለው ግለሰብ የሚገኙባቸው 120
ሰዎች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ከቦታው የደርሰን ዘገባ ያስረዳል።
ይህ በእንዲህ እያለ በሸራሮ ከተማ የሚገኙ በመንግስት የተጣለባቸን ከፍተኛ ግብር መክፈል ያልቻሉ ዜጎች
የንግድ ድርጅቶቻቸውን በመዝጋት አገር ጥለው እየተሰደዱ ነው።