Monday, September 23, 2013

በታሕታይ ማጨው የሚገኙ ገብሬዎች የአከባቢው መስተዳድር የተከልነውን ጌሾ ነቅሎ ጣለብን ፤ በማሳችንም ላይ ከብቶች በመልቀቅ አዝመራችንን አወደመ ይላሉ።



በትግራይ ማእከላዊ ዞን ፤ በታሕታይ ማይጨው የሚገኙ የእርሻ መሬት የሌላቸው ዜጎች በአከባቢያቸው አፈላልገው ባገኙት ባዶ መሬት ላይ የዘሩትን ጤፍ ከበቀለ ፤ የተከሉት ጌሾም ከጸደቀ ብሁዋላ የአከባቢው መስተዳድር በጤፍ አዝመራው ላይ ከብቶችን በመልቀቅ እንዲበላና እንዲወድም የጸደቀውንም ጌሾ ተነቃቅሎ እንዲጣል አድርጓል ። በደርጊቱ የተቆጡ ገበሬዎች ወደ ዞን አስተዳደር ሄደው ጉዳዩን ለማስረዳት ሞክረው መፍትሄ እንዳላገኙ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
በተመሳሳይ በትግራይ ሰ/ምዕራብ ዞን ፤ በመደባይ ዛና ወረዳ ፤ አከባቢ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ አዝመራቸው የወደመባቸው ገብሬዎች ማሳቸውን ዳግም ገልብጠው በማረስ በሽምብራ ለመሽፈን የሽምብራ ምርጥ ዘር እንዲሰጣቸው ለአከባቢው መስተዳድር በጠየቁበት ጊዜ አናውቅላችሁም እኛ ያወደምነው አስመራ የለም የሚል ሃላፊነት የጎደለው ምላሽ እንደሰጧቸው ቷውቋል።