በምዕራብ ትግራይ በሑመራ ከተማ ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ከስራ እጥነት መውጣት ካልቻሉት ወጣቶች አንድ የሆነው
አዱኛ የማነ ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀ ቢሆንም በመንግስት በተደጋጋሚ በሚወጡ ክፍት የስራ ቦታ የትምህርት ማስረጃውን
ይዞ ለመወዳደር ቀርቦ ሊስካለት አልቻለም። የመንግስት መ/ቤቶች
ስራ ፈላጊዎችን ባላቸው ድምር የት/ት ውጤትና ብቃት ሳይሆን በገዥው ፓርቲ አባልነትና በወገን ስለሚቀጥሩ አዱኛ ከሌሎች የተሻለ
በቂ የት/ት ማስረጃና ብቃቱ እያለው የገዥው ፓርቲ አባል ስላልሆነና ወገን ስለሌለው እንድ አንድ ዜጋ ተወዳድሮ ስራን የመያዝ መብት
ተነፍጎታል።
አዱኛ የማነ ለዓመታት ተምሮ ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ነጥብ ቢመረቅም የኢህአዴግ ስርዓት በሚከተለው ብልሹ
አስራር ምክንያት ትምህርቱን ለመቀጠልም ሆነ ስራ የማግኘት እድል ስለተዘጋበት በሙስና የተጨማለቀውን ስርዓት በመቃወም መስከረም
9/2006 ዓ/ም እራሱን እንደገደለ ለማወቅ ተችሏል።