ከስራ እየተባረሩ ያሉት ሰራተኞች ቀደም ሲል በላጭና ገምበላ በተባለ ቦታ በእርሻ ሲተዳደሩ የነበሩና ቦታው ለፋብሪካው ማረፊያ ይፈለጋል በሚል ሰበብ መሬታቸው የተነጠቁና መኖሪያ
ቤታቸውንም እንዲፈርስ በማድረግ ምንም ካሳ ሳይሰጣቸው በፋብሪካው ተቀጥረው እንዲሰሩ የተደረጉ ናቸው፣ ሰራተኞቹ ከፋብሪካው መሰናበታቸው
ብቻ የሚገልጽ ደብዳቤ እንጂ የመሰናበታቸው ምክንያት ግን ግልጽ አይደለም፣
ሰራተኞቹ ፋብሪካው ስራ ከጀመረበት እለት ጀመሮ በተለያየ ሞያ ተመድበው ፋብሪካውን ሲያገለግሉ የቆዩና በስራ
ብቃትም ይሁን በዲስፕሊን ያሳዩት ጉድለት የለም፣ ያለ ምንም መቋቋሚያ ድንገት እንዲባረሩ በመደረጉ ሰራተኞቹ ከነቤተሰቦቻቸው በችግር
ላይ ይገኛሉ፣