Thursday, September 26, 2013

በምእራብ ጎጃም ዞን የኢህአዴግ መንግስትን በመቃወም በሃይማኖት ሽፋን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲደረግ አነሳስታችሃል በሚል ሰበብ የታሰሩ ሰዎች እንዳሉ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በአማራ ክልል ፤ በምእራብ ጎጃም ዞን ስር በሚገኙ ከተሞች በማንኩሽ ፤ ፍኖተ ሰላምና ጅጋን 3 የክርስትና እምነት ተከታዮችንና 32 የእስልምና እምነት ተከታዮች የሚገኙበት በድምሩ 35 ዜጎች የእስልምና ሃይማኖትን እንደ ሽፋን በመጠቀም ህዝቡ መንግስትን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አነሳስታችሃል በሚል ምክንያት መስከረም 11,2006 ዓ/ም በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
በደበደረሰን ዘገባ መሰረት በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች ምንም ዓይነት ፖለቲካዊም ሆነ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ አልነበራቸውም ፣ በአከባቢው የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች ከግል ጥላቻ የተነሳ ባስተላለፉት የውሸት መረጃ ግለሰቦቹ መታሰራቸውን ቷውቋል፣
የኢህአዴግ ስርዓት ህዝባዊ ተቋውሞ እንዳይነሳ ካለው ስጋት የተነሳ ስርዓቱን በመቃወም የሚደረግ እንቅስቃሴ የሚመለከት የሚደርሳቸውን መረጃ ሳያጣሩ ሰዎችን በአፈሳ እየያዙ ማሰር እንደ አሰራር ተያይዘውታል፣