Sunday, September 22, 2013

በመኾኒ ወረዳ የንጹህ መጠጥ ውሃና የህክምና አገልግሎት እጥረት ምክንያት በኗሪዎቹ ላይ ከፍተኛ ችግር እያደረሰ ነው።



በትግራይ ደቡባዊ ዞን ፤ በመኾኒ ወረዳ የሚኖር ህዝብረተሰብ በንጹህ የመጠጥ ውሃና የህክምና አገልግሎት እጥረት ምክንያት ከወሩ-አባየ ከተባለ አከባቢ ላጤ ከተባለ ልዮ ቦታ ጥራቱን ያልጠበቀ የጉድጓድ ውሃ ለመጠቀም ይገደዳሉ ። በዚሁ ጥራት የጎደለው ውሃ ምክንያትም ህጻናትና እናቶች የሚገኙባቸው በርካታ የአከባቢው ኗሪዎች ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታ መጋለጣቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
የወረዳው ጤና ጣብያ በቂ የህክምና መሳሪያ ፤ መድሃኒትና የሰው ሃይል የለውም። በጢና ጣብያው የሚገኙ የጢና ባለሞያዎች ከወረዳው ህዝብ ጋር ሲነጻጸር ቁጥራቸው እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ በርካታ  እናቶችና ህጻናት በወሊድ ጊዜ ህይወታቸውን ያጣሉ።
    ይህ በእንዲህ እያለ በወረዳዋ የሚገኙ የስርዓቱ ካድሬዎች ህዝቡን ግምገማ ፤ፓኬጅና የአንድ ለአምስት አደረጃጀት ወዘተ በሚል ፋይዳ በሌለው ስብሰባ ጠምደው ስለሚይዙት እለታዊ ህይወቱን በአግባቡ መምራት ተስኖታል ። ድርጊቱ የሚቃወሙ የአከባቢው ኗሪዎችም ጸረ-ልማት የሚል ስም እየተለጠፈባቸው በገንዘብ ከመቅጣት ጀምሮ እስር ቤት እስከ መክተት በሚደርስ ቅጣት እንደሚቀጡ ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።