Thursday, September 26, 2013

በአዊ ዞን የሚገኙ መምህራን ተማሪዎቻቸውን እንዲሰልሉ ስልጠና እንደተሰጣቸው ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን የሚገኙ መምህራን የዓቅም ግምባታ ስልጠና ትወስዳላችሁ በሚል ከመስከረም 7 እስከ መስከረም 12/2006 ዓ/ም በተሰጣቸው ስልጠና አስተማሪዎቹ በተመደቡበት ት/ቤት ሁሉ የእስልምና አክራሪነትም ሆነ ሌላ ዓይነት ተቋውሞ በተማሪዎች እንዳይቀሰቀስ ክትትል እንዲያደርጉ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ስልጠና ተሰጥታቸዋል፣
ይህ በእንዲህ እያለ ከቻግኒ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው የመኪና መንገድ ከመስከረም 9,2006 ዓ/ም ጀምሮ ከአገልግሎት ውጭ እንዲሆን በመደረጉ በመንገዱ ሲገለገሉ የነበሩ ነጋዴዎችና የአከባቢው ኗሪዎች በተከሰተው የትራንስፖርት አገልግሎት መተጓጎል ምክንያት ችግር ላይ መውደቃቸውን ቷውቋል፣