ሰላማዊ ሰልፉ የተካሄደው መስከረም 12/2006 ዓ/ም ሲሆን በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ የአ/አበባ ከተማ ኗሪዎች
ተሳትፈዋል፣ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ሲስተጋቡ ከነበሩት መፈክሮች መካከል የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ! ፤ ዜጎችን ከቀያቸው ማፈናቀል ይቁም!
፤ መንግስት በሃይማኖት ላይ እጁን ማስገባት ያቁም! ህግ ይከበር! ፤ የህዝቡ ድምጽ ይሰማ ! የሚሉ ይገኙበታል፣
ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን ለማድረግ የጠየቀው በመስቀል አደባባይ ሲሆን በኢህአዴግ ስርዓት የተሰጠው
ፈቃድ ግን በጃን ሜዳ እንዲደረግ ነበር፣
ነገር ግን የፓርቲው አመራር ለማን ተፈቅዶ ለማን ይከለከላል በማለት በመስቀል አደባባይና በአራት ኪሎ በመንቀሳቀስ
ሰላማዊ ሰልፉን ስኬታማ በሆነ መንገድ ማካሄድ ችሏል፣
በመጨረሻም በሰላማዊ ሰልፉ ለተገኙት ሁሉም ተሳታፊዎች አንድነት ፓርቲ በጠራውና መስከረም 19/2006 ዓ/ም
ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ሰላማዊ ሰልፍ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርባል፣