Thursday, September 26, 2013

በመከላከያ ሰራዊት የሚገኙ የብሄረ ትግራይ ተወላጆች ቁጥር ከሚገባው በታች በመውረዱ የብሄሩን ተዋጽኦ ከፍ ለማድረግ አዲስ የአመላመል አሰራር እንደሚኖር የደረሰን ዘገባ ያመክታል፣



በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ያለውን የብሄረሰቦች ተዋጽኦ ስብጥር ሲታይ የትግራይ ብሄር ተወላጆች በተለያዩ ምክንያት እየተመናመነ ስለመጣ ችግሩ ከወዲሁ ታይቶ ቶሎ እንዲስተካከል የትግራይ ክልል በጠየቀው መሰረት የተከሰተውን ክፍተት ለመሸፈን የተለየ የአመላመል አሰራር ማስፈለጉን ቷውቋል፣
የኢህአዴግ አመራሮች የመከላከያ ሰራዊትን አስመልክተው ባካሄዱት ስብሰባ የብሄረ ትግራይ ተዋጽኦ ለምን ከሚፈለገው በታች አሽቆለቆለ የሚል ነገር በሰፊው ተነጋግሮውበታል ፣ ከክልሉ የተመለመሉ ወጣቶች በምልመላው ወቅት የትምህርት ደረጃቸውን የሚመጥን ሞያዊ ስራና የትምህርት እድል እንደሚሰጣቸው የተገባላቸውን ቃል ተግባራዊ ባለመሆኑና ብዙ ዓመት ታግለን በሌላ ብሄር ተዋጥን በሚል ገሚሶቹ እግራቸው ወደ መራቸው ሲኮበልሉ ገሚሶቹ ደግሞ የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር በመቀላቀላቸው ለቁጥሩ መመናመን እንደ ምክንያትነት ተጠቅሳል ፣
የተከሰተውን ክፍተት ለመሸፈን ለአዳጊ ክልሎች በልዩ የሚሰጠውን የአመላመል አሰራር በተመሳሳይ በትግራይ ክልልም ተግባራዊ እንዲሆን በማድረግ ለውትድርና የሚመለመሉ ወጣቶች የት/ት ደረጃቸው ወደ 7ኛ ክፍል ዝቅ በማድረግ ምልመላውን ለማፋጠን የክልሉ ካድሬዎችና የሰራዊት አዛዦች በመሯሯጥ ላይ ይገኛሉ፣