Wednesday, September 18, 2013

በሸራሮ ከተማ የሚገኙ የህወሓት-ኢህአዴግ ካድሬዎች በኢህአዴግ ስርዓት ብልሹ አሰራር ቅር የተሰኘውን የከተማዋ ኗሪ ህዝብን ለማግባባት እየሞከሩ ነው።



የታሕታይ አድያቦ ወረዳ የህወሓት ተወካይ የሆኑት አቶ ዳኛቸውና የሸራሮ ከተማ አስተዳዳሪ ወዲ አወጣሽ በህወሓት-ኢህአዴግ ስርዓት የተማረረውን የሸራሮ ከተማ ኗሪ ህዝብን ተቋውሞ ለምለዘብ ሲሉ መስከረም 5 እና 7,2005 ዓ/ም መላው የከተማዋን ኗሪ በመሰብሰብ የአሰራር ለውጥ እንደተደረገ ፤ በህዝቡ ተቀባይነት ያልነበራቸው የመንግስት ሽሟምንቶች እንደተዛወሩና በምትካቸው ሌሎች እንደተመደቡ በመግለጽ የተሸሙትን አዲስ የመንግስት ሽሟምንቶችም በህዝቡ ፊት ቀርበው እንዲተዋወቁ በማድረግ ሲመጻደቁ እንደነበር ከከተማዋ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት የጸረ-ህዝቡ ስርዓት ካድሬዎች ህዝቡን በስብሰባ ጠምደው በመያዝ በከተማዋ የመስተዳድር አካላት ለውጥ ስለተደረገ ካሁን ብሁዋላ ማንኛውም ሰው የድርጅት አባል እንዲሆንና በማይክሮ ፋይናንስ ገንዘብ እንዲቆጥብ ቅስቀሳ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይህንን ለማድረግ የድርጅቱ አባላትና በአንድ ለአምስት አደረጃጀት የተደራጁ ሁሉ ጠንክረው በመስራት በድርጅቱ የተሰጣቸውን ስራ መወጣት ይጠበቅባቸዋል በማለት የድርጅቱን መመሪያ የሚያደናቅፍ ሰው ጸረ-ልማት መሆኑ ታውቆ አስፈላጊውን እርምጃ ይወሰድበታል ዚሉ መናገራቸውን ቷውቋል።
ቀደም ሲል የከተማዋ አስተዳደር የነበረው አቶ ጥላሁን በርሀ በህዝብ ተቋውሞ ከሃላፊነቱ ተነስቶ ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወር መደረጉን የሚታወቅ ነው።