Thursday, September 26, 2013

በወልቃይት እየተገነባ ባለው የስኳር ፋብሪካ አገልግሎት እንዲውል ተብሎ በሁለት ተሽከርካሪዎች ተጭኖ የተላከ ስሚንቶ ፤ ተንዲኖና ጣውላ ወደ ፋብሪካው ሳይደርስ ለነጋዴዎች መሸጡን ቷውቋል፣



ንብረትነቱ የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የሆነ ኮድ 3 ሰሌዳ ቁጥር 00529 አማ የሆነ አንድ ተሽከርካሪ ከነተሳቢው ጭኖት የነብረ ተንዲኖና ስሚንቶ በባህርዳር ከተማ በአቶ መንግስቱ መጋዝን የተራገፈ ሲሆን ፥ ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 13045 ኢት የሆነ ሌላ ተሽከርካሪ ጭኖት የነበረ ጣውላ ደግሞ በባህርዳር ከተማ በሚገኝ የአቶ ገ/ሚካኤል መጋዘን ሲራገፍ በአከባቢው ህዝብ ትብብር መስከረም 9,2006 ዓ/ም እጅ ከፈንጅ መያዙን ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያስርዳል፣
የፋብሪካው ስራ አስከያጅ ለፋብሪካው ተብሎ የሚላከውን ንብረት በባህርዳር ከተማ ለነጋዴዎች ሲሸጡ በተደጋጋሚ መያዛቸው የሚታወቅ ነው፣