Thursday, September 26, 2013

የትግራይ ክልል መንግስት በክልሉ የሚገኙ ገበሬዎችን ለመስኖ እርሻ የሚውል ማዳበሪያ እንዲገዙ እያስገደደ ነው፣



በመቐለ ከተማ አከባቢ የሚገኙ በመስኖ እርሻ የተሰማሩ ገበሪዎች መንግስት ያቀረበውን ማዳበሪያ ገዝተው መጠቀም እንዳለባቸው ይህን የማይተገብሩ ከሆነ መሬታቸው ተነጥቀው ለሌላ ሰው ተላልፎ እንደሚሰጥ ማስጠንቀቅያ ተሰጥታቸዋል፣
እንደ ገበሬዎቹ አባባል የማዳበሪያ ዋጋ በጣም በመወድዱ የተነሳ ማዳበሪያ መጠቀም ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን እንደ ተለመደው ማዳበሪያ ሳይጠቀሙ መዝራትን ይመርጣሉ፣