በትግራይ ክልል እየታየ ያለ እራስን የማጥፋት ተግባር ዋና መነሻ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው፣ ዜጎች
ጥረው ግረው እራሳቸውን ለመለወጥ ከፍተኛ ትግል ቢያደርጉም ሁሉም ነገር በወገንና በጉቦ ስለሚሰራ አላስፈላጊ አድልዎና ጫና ስለሚደረግባቸው
በሁኔታው ተስፋ የቆረጡ ወጣቶች እራሳቸውን ለማጥፋት ይገደዳሉ፣
በዚሁ ሳምንት እራሳቸውን ካጠፉት ዜጎች ለመጥቀስ
-ቴዎድሮስ በየነ ኗሪነቱ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 03 በመካኒክነት ሞያ ሲተዳደር የነበረ ከአቅሙ
በላይ የሆነ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍል ተወስኖበት ውሳኔውን ዳግም እንዲታይለት ጠይቆ መፍትሄ በማጣቱና ስራው እንዲያቆም በመደረጉ
እራሱን አጥፍታል፣
-ተማሪ እዮብ አማረ ኗሪነቱ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 04 መስከረም 10,2006 ዓ/ም እራሱን ያጠፋ
-ሙላው የተባለ ወጣት በመቐለ ከተማ ከሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ የ 3ኛ ዓመት ተማሪ የነበረ የትምህርት ምስክር
ወረቀት እንዲሰጠው ጠይቆ በመከልከሉ ምክንያት እራሱን የገደለ
ከዚህ ቀደም ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀ ኗሪነቱ በሑመራ ከተማ የሆነ አዱኛ የተባለ ወጣት በተመሳሳይ
ችግር እራሱን መግደሉን መዘገባችን የሚታወቅ ነው፣