Thursday, September 12, 2013

የህወሓት መካከላኛ አመራሮች የስራ እቅድ ለመገምገም በአ/አበባ ከተማ ያደረጉት ስብሰባ ያለመግባባት ተጠናቀቀ።



ህወሓት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ የመጣ ሲሆን ድርጅቱን ካጠላበት የመበታተን ደመና እራሱን ለማዳን ሲባል የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ፋታ በማይሰጥ ስራ እራሳቸውን ጠምደዋል ። በከፍተኛ አመራሩ የሚነሱ ሃሳቦችና የሚተላለፉ መመሪያዎች ከታች ባሉ አመራሮች ተቀባይነት እያጡ ውድቅ ስለሚሆኑ አመራሩ ስሜት ውስጥ እየገባ ከያዘው አጀንዳ እየወጣ ሲነታረክ የተያዘው ስብሰባ ያለውጤት መበተኑን ቷውቋል።
በህወሓት ከፍተኛ አመራሮች የተከሰተው አለመግባባት በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦችም ውስጥ ተጋብቶ የሰራዊቱን አደረጃጀትንና አሰራርን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል ።
ህወሓት በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በእንዲህ ዓይነቱ ትርምስ ውስጥ ሲገባ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኖ ክስተቱ የድርጅቱ ውድቀትን የሚያመላክት ቢሆንም የህወሓት አመራሮች ህዝብን ለማደናገርና አለን ለማለት በማስመሰል የፕሮፖጋንዳ ስራ ተጥምደዋል ። የትግራይ ህዝብ ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ የራሱን አማራጭ ለመውሰድ መንገዶችን እያመቻቸ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።