Thursday, September 12, 2013

የአ/አበባ ከተማ ኗሪ ህዝብን በአንድ ለአምስትና ሰባት ለሰላሳ በሚሉ አደረጃጀት ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ እየተደረገ ነው።



ኢህአዴግ አንድ ለአምስትና ሰባት ለሰላሳ የሚለው አደረጃጀት በአ/አበባ ከተማ ከጀመረ የቆየ ቢሆንም አሁን በተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶችና የሃይማኖት ነጻነት ይጠበቅ በሚሉ እየተደረገ ያለው መነሳሳትና ሰላማዊ ሰልፍ ለማሰናከል ሲባል ታስቦ የተደረገ ሲሆን ፥ በዚሁ አደረጃጀት የተደራጁ ሰዎች በየጊዜው እየተገናኙ መረጃ በመለዋወጥ የተለያየ እንቅስቃሴ ካለም ከአመራሩ ጋር በመነጋገር ይወስናሉ ። ግዴታውን የማይወጣ ግለሰብ ካለም ህግን እንደጣሰ ተቆጥሮ በአደረጃጀቱ ውሳኔ እንዲሰጠው ይደረጋል።
መንግስት እነዚህን አደረጃጀቶች የስለላ መረቡ መሰረት ለማድረግ ባለው ፍላጎት የስርዓቱ ካድሬዎች ቅድሚያ ሰጥተው አደረጃጀቶችን እንዲያጠናክሩ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው ።