ባለፈው የበጀት ዓመት 2005 ዓ/ም ለህዝባዊ አገልግሎት ለሚሰጡ ፕሮጀችቶች ግምባታ ፤ ጥገናና ማስፋፊያ
ተብሎ ከተመደበው በጀት 120 ሚልዮን ብር በተፈለገው ስራ ሳይውል የባከነ ሲሆን የቢሮው ሃላፊዎች የባከነውን ገንዘብ ለማጣራት
እያካሄዱት ባለ ስብሰባ በየበታች ሰራተኞች እንደተጠፋፋ አስመስለው ለማቅረብ ሞክረዋል፣ የበታች ሰራተኞቹ በበኩላቸው ዘርፋው የተፈጸመው
በቢሮው አመራሮች ነው የሚል ነገር በማንሳታቸው በመሃከላቸው ከፍተኛ ውጥረት መፍጠሩን ቷውቋል፣
ስብሰባው ከተጀመረ ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን በአመራሩና በሰራተኞች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ከፍተኛ አመራሮች
ጉዳቸው ለመደበቅ ሲሉ ሁኔታው በሚድያ እንዳይዘገብ ማንኛውም ሰራተኛ ወደ ስብሰባው እስኪርቢቶና ወረቀት ይዞ እንዳይገባ መከልከሉንና
ፍተሻ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል፣
በቢሮው አመራሮችና ሰራተኞች መካከል የተነሳው አለመግባባት ወደ ከፍተኛ ደረጃ በመድረሱ ግጭት እንዳይፈጠር
ቢሮው በጸጥታ ሃይሎች እየተጠበቀ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣