በትህዴን የተዘጋጀና “ኢትዮጵያን ለማዳን የኢህአዴግን ስርዓትን በመቃወም እንደራጅ!!” በሚል ርእስ ለመላው
የኢትዮጵያ ህዝብ የቀረበ ጥሪ የያዙ በራሪ ወረቀቶች መስከረም 19,2006 ዓ/ም ለሊት በአ/አበባ ከተማ ጎዳናዎች መበተኑን ከቦታው
የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
በራሪ ወረቀቱ “ የኢትዮጵያ ህዝብ ለሰላም ፤ ዴሞክራሲ ፍትህና እኩልነት መረጋገጥ ላለፉት ብዙ ዓመታት
ያካሄደውን ትግልና የከፈለው መስዋእትነት ግቡን ሳይመታ ለግል ጥቅማቸው እንጂ ስለ ሃገርና ህዝብ ቅንጣት ስሜት በሌላቸው ጥቂት
አምባገነኖች መነጠቁንና እነሱ ያዘዙትን ተቀብሎ ከመሄድ ውጭ ሃሳቡን በነጻ እንዳይገልጽ አፍነው በመያዝ የነሱ መሳሪያ ሆኖ እንዲኖር
ስላደረጉ ፥ አፈናውን በመቃወም በብሄርና ሃይማኖት ሳትለያይ በአንድነት እያካሄድከው ያለውን እንቅስቃሴ ትህዴን ይደግፋል እስከ
መጨረሻም ከጎንህ ይቆማል “ በማለት ያረጋግጣል፣
ገና ከጠዋቱ የኢህአደግን ስርዓት በሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ መንገድ ትግሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል
የተገነዘበው ትህዴን ከ 12 ዓመታት በፊት ለካቲት 19,1993 ዓ/ም ዱር ቤቴ ብሎ ጸረ-ህዝቡን ስርዓት በሚገባው ቋንቋ ለማነጋገር
ህዝቡን እያደራጀ የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፣
ትህዴን በአሁኑ ጊዜ የትግል አድማሱን በማስፋት ከተለያዩ የኢህአዴግ ስርዓትን ከሚቃወሙ ድርጅቶች ፤ ማህበራትና
ግለሰቦች ግንኝነት በማድረግ ዓላማውን ሰማሳካት በመረባረብ ላይ የሚገኝ ሲሆን በአ/አበባ ከተማ የተበተነው በራሪ ወረቀትም የትግሉ
አንድ አካል መሆኑን ከትህዴን የህዝብ ግንኝነት ቢሮ የተገኘ ዝገባ ያስረዳል፣