ሰብሰባው በምእራብ ጎጃም ዞን አስተዳዳሪና በአቶ አዲሱ ለገሰ እየተመራ በፍኖተ ሰላም ከተማ ከመስከረም
10/2006 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሄደ ሲሆን ፥ በክልሉ የሚገኙ የሁሉም ወረዳ የመስተዳድር አካላት አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው
፣ የስብሰባው አጀንዳ በ2007 ዓ/ም ስለሚደረገው ምርጫ የተመለከተ ሲሆን ምርጫውን የማሸነፍ ጉዳይ ለኢህአዴግ የሞት ሽረት ጉዳይ
ስለሆነ የድርጅቱ ካድሬዎችና አባላት ጠንክረው የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በምርጫው በአሸናፊነት ለመውጣት ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ
ለማስገንዘብ መሆኑን ቷውቋል፣
የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከሩ በመምጣታቸው በአንድ
ለአምስት አደረጃጀት ፤ በገንዘብ ይሁን በሌላ ጥቅማ ጥቅምና የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም በኢህአዴግ ላይ የሚደረገውን የተቃውሞ
እንቅስቃሴ አሽንፈን ለመውጣት ቃል መግባት ይገባል ሲሉ ስብሰባውን በመምራት ላይ የነበሩ የስርዓቱ ባለስልጣናት መናገራቸውን ቷውቋል፣