Wednesday, October 2, 2013

በትግራይ ክልል በሾፌርነት ሞያ ስልጠና እየሰጡ ያሉ ድርጅቶች ከሌላ ክልል ለሚመጡና በሞያው ለመሰልጠን የሚፈልጉ ሰዎችን ተቀብለው ስልጠና እንዳይሰጡ በመንግስት መታገዳቸውን ከመቐለ ከተማ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በደረሰን ዘገባ መሰረት በክልሉ የሚገኙ በሹፈርነት ሞያ ስልጠና በመስጠት የተሰማሩ ድርጅቶች ከመንግስት ባለስልጣናት በወረደው ፖለቲካዊ ትእዛዝ መሰረት ከክልሉ ካልሆነ ከሌላ ክልል ለሚመጡ ኢትዮጵያዊያን ስልጠና እንዳይሰጡ ታግደዋል፣ የእገዳው ዋና ምክንያት ህዝብን በመለያየት በመሃከላቸው ቅራኔ ፈጥሮ እርስበርሳቸው በጥላቻ እንዲተያዩ በማድረግ የኢህአዴግን ስርዓት እድሜ ለማራዘም ነው፣
በሞያው የተሰማሩት ሰዎች በበኩላቸው የሃገሪቱን ህግ የነጻ ገበያ ኢኮኖሚን የሚፈቅድ ስለሆነ ሞያውን ለመማር የሚፈልግ ማንኛውንም ግለሰብ ከፈለገው አከባቢ ይምጣ መሰልጠን እስከፈለገ ድረስ ስልጠናውን መስጠት ለነጋዴው የሚመለከት ጉዳይ እንጂ መንግስትን የሚመለከት አይደለም፣ መንግስት ህግን ማክበርና ማስከበር ሲገባው በዜጎች ላይ አላስፈላጊ ጫና ማድረግ የለበትም በማለት በስርዓቱ ባለስልጣናት የተሰጠውን ፖለቲካዊ ትእዛዝ በመቃወም ሞያውን መማር የሚፈልግ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ተቀብለን እናሰለጥናለን ሲሉ አቋማቸውን ገልጸዋል፣