Wednesday, October 2, 2013

በአስገደ-ጽምብላ ወረዳ ፤ በእንዳባ ጉና ከተማ የሚገኙ የፖሊስ አዛዦች በህዝቡ መካከል ግጭት ለመፍጠር እያሰሩ ነው፣



በትግራይ ሰ/ምእራብ ዞን ፤ በአስገደ ጽምብላ ወረዳ አሰፋ ይሕደጎ በተባለ ሰው የሚመራ አንድ ጋንታ የፖሊስ ሃይል በወረዳዋ በባህላዊ መንገድ ወርቅ እንዲያመርቱ የተፈቀደላቸውን ሁለት መቶ ወጣቶችን በመያዝ ራህዋ በተባለ ልዩ ቦታ ይደርሳል፣ ወጣቶቹ በቦታው እንደደረሱ ወዲያውኑ ቁፋሮ ይጀምራሉ ፣ በሁኔታ የተቆጡ የአከባቢው ኗሪዎች መሬታችንን አናስቆፍርም በማለት የታጠቁትን ብረት በማንሳትና አንድ ላይ በመሆን ወጣቶችን አጅቦ ከመጣው የፖሊስ ሃይል ጋር ፊት ለፊት ተፋጠጡ ፣ ሁኔታው ያላማራቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት ወደ አከባቢው የተላኩት የፖሊስ አባላትና ወጣቶቹ በመጡበት አካሃን በሦስት ተሽከርካሪዎች ተጭነው አከባቢውን ለቀው ቶሎ እንዲወጡ ለማዘዝ ተገደዋል፣
የራህዋ አከባቢ ኗሪዎች በወረዳዋ የፖሊስ አዛዥ የተፈጸመውን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ከአንድ የሽፍታ መንጋ እንጂ ከመንግስት አካላት የሚጠበቅ አይደለም በማለት መንግስት ህግና ስርዓትን ማስፈን ሲገባው ከወንድሞቻችን ጋር ሊያገጨን ይሞክራል ሲሉ ድርጊቱን በማወገዝ በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፣