Tuesday, October 1, 2013

በጃዊ ወረዳ በኢህአዴግ ስርዓት ላይ ተቋውሞ አነሳስታችሃል በሚል ሰበብ በርካታ ወጣቶች ታሰሩ፣



በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ በጃዊ ወረዳ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ ወጣቶች በኢህ አዴግ ስርዓት የሚፈጸሙትን ጸረ-ህዝብ ተግባራትን በመቃወማቸው ምክንያት በአከባቢው የመስተዳድር አካላትና በጸጥታ ሃይሎች ጸረ-ልማት ፤ አሸባሪዎች የሚል ስም እየተሰጣቸው በየእስር ቤቱ እየተወረወሩ ነው፣
በያዝነው ሳምንት ብቻ የአከባቢውን ህዝብ መንግስትን በመቃወም እንዲነሳሳ ቀስቅሳችሃል በሚል ሰበብ በፖሊስ አባላት ተይዘው ከታሰሩት ወጣቶች መካከል።-
·       አቶ አይሸሹ አዲሱ
·       አቶ ጌትነት ፋንታሁን
·       አቶ ጌታው ገነት
·       አቶ አብረት በቀለ
·       አቶ አብዮት ማሙየ
·       አቶ አበባው ትእዛዙ
የሚገኙባቸው ሲሆን ምንም ወንጀል ሳይፈጽሙ በየእስር ቤቱ ታጉረው በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ፣