መስከረም 19/2006 ዓ/ም በአንድነት ፓርቲ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ “የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት” በሚል
መሪ ቃል ስር ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ እስከ አንድ መቶ ሽህ የሚደርስ የአ/አበባ ከተማ ኗሪ ተሳታፊ ሆኖዋል፣ በሰላማዊ ሰልፉ ሲስተጋቡ
ከነበሩት መፈክሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፣
-ህዝብን እያሸማቀቁ መግዛት አሸባሪነት ነው!
-ኢህአዴግነት ከኢትዮጵያዊነት አይበልጥም!
-ኢትዮጵያ አንድ ናት!
-ሙስና የኢህአዴግ ስርዓት መገለጫ ነው!
-መብታችንን ከኢህ አዴግስርዓት አንጠብቅ!
-የኢህአዴግ ስርዓት እስኪወገድ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል!
-የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!
አንድነት ፓርቲ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ የጠየቀው በመስቀል አደባባይ የነበረ ቢሆንም የስርዓቱ
ባለስልጣናት ስላልፈቀዱ የአንድነት አመራር ህዝቡን በሚገባ በማስተባበርና የሚፈለገውን መልእክት በማስተላለፍ ሰላማዊ ሰልፉን በስኬት
አጠናቋል፣
የስርዓቱ ባለስልጣናት ብዛት ያላቸው የፖሊስ አባላት በማሰማራት ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ሰላማዊ ሰልፉ
ሲያመራ የነበረውን ህዝብ ለማገት ሞክረዋል፣ ተሰማርተው ከነበሩት የፖሊስ አባላት መካከል ትእዛዝ ሆኖብን ነው በማለት ሲናገሩ ተደምጠዋል፣
ይህም ስርዓቱ ምን ያህል ስጋት ውስጥ መግባቱን የሚያመላክት ነው፣