የክልሉ መንግስት የሽብር አደጋ እንዳለ በማስመሰል ህዝብን ለመቆጣጠር ካለው ፍላጎት የተለያዩ ቅስቀሳዎችን
ሲያካሂድ ቆይቷል፣ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለስርዓቱ ስጋት ናቸው በሚባሉ ከተሞች መውጭና መግቢያ በሮች ላይ በርካታ አዳዲስ
ኬላዎችን በመክፈት ከከተማ የሚወጡና የሚገቡ ሰዎችን በጥብቅ መፈተሽ ጀምራል፣
ኬላ በመክፈት የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገባቸው ካሉት ከተሞች መካከል ውቕሮ-ክልተ ኣውላዕሎ ፤ ኣጉላዕ
፤ ዛላምበሳና ሌሎች ያልተጠቀሱ ከተሞች ይገኑበታል፣ የመንግስት ተቋማትና ጽ/ቤቶችም የተጠናከረ ትበቃ እየተደረገላቸው መሆኑን ቷውቋል፣
ኢህአዴግ ከራሱ ውስጣዊ ስጋት በመነሳት የህዝብን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ሲል በህዝቡ ላይ ያነጣጠረ የሽብር
ተግባር እንዳለ በማስመሰል እያንዳንዱ ዜጋ እራሱንና አከባቢውን እንዲጠብቅ በማለት ባስተላለፈው መመሪያ ህዝቡን እርስ በእርሱ እንዲጠራጠር
በማድረግ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ከቶቷል፣