Friday, November 15, 2013

በስብሰባ ብዛት የተሰላቹ የጃዊ ወረዳ ኗሪዎች ዕለታዊ ስራችንን በአግባቡ መስራት አልቻልንም አሉ፣




በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን ፤ የጃዊ ወረዳ ኗሪዎች በኢህአዴግ ካድሬዎች በተጠራ ስብሰባ በመጠመዳቸው የአከባቢው ገበሬዎች ምርታቸውን በጊዜ መሰብሰብ ባለመቻላቸው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ለኪሳራ እየተዳረጉ መሆናቸውን ቷውቋል፣
ስብሰባው የተመራው በወረዳዋ አፈ ጉባኤ አቶ ንጉሴ ወርቄ ሲሆን  የስብሰባው አጀንዳም የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የሚል ሆኖ ያለፈቃድ ወረቀት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እንደማይቻልና ሊታሰሩም እንደሚችሉ በመግለጽ ተሰብሳቢውን ሊያስፈራራ ሞኩራል፣ ነገር ግን የህዝቡ ዓመት ሙሉ ለፍተን ያፈራነው ገና ከማሳው ያልተሰበሰበ አዝመራ አለን ስብሰባው ቶሎ ያብቃ በማለት ጥያቄ ቢያቀርብም ስብሰባውን ሲመራ የነበረ ካድሬ ሊቀበላቸው ስላልቻለ ግርግር ተነስቶ መግባባት በማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በባህርዳር ከተማ በሚገኘው የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሰራተኞች የደምዎዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸው የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ጥቅምት 15,2006 ዓ/ም ያካሄዱ ሲሆን ከመሃከላቸው 5 ሰራተኞች አድማ አስነስተዋል በሚል በከተማዋ ፖሊስ ታፍነው ተወስደዋል፣ እስካሁን ድረስም አድራሻቸው በውል እንደማይታወቅ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣