በክልሉ በሁሉም ከተማዎች የሚገኙ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ የቀን ሰራተኞች ከሚያገኙት ገቢ 15% ለመንግስት
ግብር እንዲከፍሉ የሚያመለክት ማዘዣ ጥቅምት 12,2006 ዓ/ም የወረደውን መመሪያ ተከትሎ ሰራተኞቹ ተቃውማቸውን በመግለጽ ላይ
ናቸው፣
በተለይም በሑመራና በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሚገኙ በጉልበት ስራ የሚተዳደሩ የቀን ሰራተኞች የወረደውን
መመሪያ ሰራተኛው ያልተወያየበት በጫና በማስፈራራት ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረግ እንቅስቃሴ ተቀባይነት የለውም በማለት ውድቅ አድርገውታል፣
የወረደውን መመሪያ ግንባር ቀደም ከተቃወሙት ሰራተኞች መካከል ፍርያት መኮነን ፤ክፍሎም ግደይ ፤ ዳንኤል
ወዲ መቐለ፤ የማነ(የመከላከያ አባል የነበረ) አሸናፊና ሞገስ የተባሉ ይገኙበታል፣