Saturday, November 2, 2013

ዘለቄታዊ መፍትሄ ያጣው የመቐለ ከተማ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እየተባባሰ መጣ፣




የመቐለ ከተማ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም ጥናት እየተደረገ ነው የሚል መሸንገያ ካልሆነ በትክክል ችግሩ በሚመለከተው አካል ቱክረት አግኝቶ ዘላቂ መፍትሄ ሊደረግለት አልቻለም፣ በዚህም መላው የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ጥራቱን ያልጠበቀ ውሃ ለመጠቀም በመገደዱ ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች ሲጋለጥ ቆይቷል፣ በአሁኑ ጊዜም በመጠኑ ይገኝ የነበረ ውሃ እየቀነሰ በመምጣቱ የከተማዋ የውሃ ችግር ከመቸውንም ጊዜ በላይ ተባብሳል፣
የመቐለ ከተማ ኗሪዎች መንግስት በከተማዋ የሚታየውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር ለመፍታት ለምን ቅድሚያ ቱክረት ሰጥቶ አይሰራም በማለት ላቀረቡት ጥያቄ የከተማዋ መስተዳድር ሲመልስ መስተዳድሩ የከተማዋን የውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ገና ጥናት እየተደረገ እንደሆነና በአሁኑ ጊዜ ግን ለከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የኮብል ስቶን ንጣፍ ስራን ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ነው ሲል በተለመደው መንገድ ሲዘላብድ ተደምጧል፣