የደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የኢህአዴግን ስርዓት በመቃወም ጥቅምት 8,2006 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ
ያካሄዱ ሲሆን የሰላማዊ ሰልፉ ዓላማ ለዩኒቨርሲቲው ተብሎ የሚመደብ በጀት ለተመደበለት ዓላማ ሳይውል ተመልሶ ለመንግስት ፈሰስ ስለሚደረግ
በመማር ማስተማር ሂደት ላይ ችግር እየፈጠረ ነው በሚል መሆኑን ቷውቋል፣
ዩኒቨርሲቲው
ለተማሪዎቹ የሚያቀርበው ምግብ ጥራት የሌለው በመሆኑ በዚህም ተማሪዎቹ በአግባቡ ትምህርታቸውን መከታተል እንዳልቻሉ በተለይም በዩኒቨርሲቲው
ተሰጥቷቸው የነበረው ብርድ ልብስ ስልተነጠቁ የአከባቢውን ብርድ መቋቋም አልቻሉም፣ በተደጋጋሚ በተማሪዎች ላይ እየተፈጸመ ያለው
አስተዳደራዊ በደል መፍትሄ እንዲደረግለት በመጠየቅ ተማሪዎቹ የጀመሩትን አድማ አጠናክረው የቀጠሉበት ሲሆን ጥያቅያቸው ካልተመለሰ
የመማርና የማስተማር ሂደቱ ሊሰናከል እንደሚችል የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣