Saturday, November 9, 2013

ለወልቃይት የስኳር ፋብሪካ ልማት ፕሮጀክት የሚላከው ንብረት በድርጅቱ ሃላፊዎች እንደሚዘረፍ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣




በወልቃይት እየተገነባ ላለው የስኳር ልማት ፕሮጀችት አገልግሎት እንዲውል ተብሎ በኮድ ቁጥር ኢት-3,የሰሌዳ ቁጥር 08956 የተላከ ነዳጅ ጥቅምት 21,2006 ዓ/ም የፕሮጀክቱ ሃላፊ ከነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር አየር ባየር የሸጠው ሲሆን ድርጊቱን የተቃወሙ የፕሮጀክቱ የንብረት ክፍል ሃላፊ አቶ አለማዮሁ ሃይለ ከስራ መባረሩን ቷውቋል፣
ቀደም ሲል ለፕሮጀክቱ ግምባታ እንዲውል በሚል የተላከ ስሚንቶ ፤ ቴንዲኖና ነዳጅ በፕሮጀክቱ ሃላፊዎች እየተዘረፈ በሸረ-እንዳስላሰና በባህርዳር ከተማ ለነጋዴዎች ሲሸጥ እጅ ከፈንጅ ተይዞው ሲያበቁ ጉዳዩ ሳይጣራ ነጻ መለቀቃቸውን የሚታወስ ነው፣