Tuesday, November 5, 2013

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የፖሊስ አባላት ጨለማን ተገን በማድረግ ስቆችን እንደሚዘርፉ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣




በጎንደር ከተማ የተለያዩ ስቆችንና ማከፋፈያ ድርጅቶችን በመክፈት በንግድ ስራ ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ወገኖች የንግድ ድርጅቶቻቸው ያሉበት አከባቢ የፖሊስ ሃይል የማይለይበትና ሌሊትን ጨምሮ ሙሉ ጥበቃ የሚደረግለት እያለ ጥቅምት 20,2006 ዓ/ም ሌሊት የንግድ ድርጅቶቹ መዘረፋቸው ለኗሪው ግራ አጋብቷል ፣ ንብረታቸው የተዘረፈባቸው ነጋዴዎች ወንጀሉ በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ የፖሊስ አባላት እጅ አለበት ሲሉ ቅሬታቸውን ለሚመለከተው አካል ገልጸዋል፣
የከተማዋ የፖሊስ አዛዦች በቡኩላቸው ክሱ መሰረት የለውም ፖሊስ የህዝብን ንብረት የሚጠብቅ እንጂ የሚዘርፍ አይደለም በማለት የቀረበባቸውን ክስ ውድቅ አድርገውታል፣
የንግድ ድርጅቶቻቸው ከተዘረፈባቸው ነጋዴዎች መካከል
1-አቶ ሓሰን ኢብራሂም ከ 90 ሽህ በላይ የሚገመት ንብረት
2-አቶ ከድር ሓቢብ ከ 150 ሽህ በላይ የሚገመት ንብረት
3-አቶ ጸሃየ ተክለ ከ 10 ኩንታል በላይ ስኳርና ሌሎች ሸቀጣ ሸቀጦችን
4-አቶ ፋንታሁን እንዳርጌ ከ 14 ኩንታል በላይ በርበሬ